የእርስዎ ቤተ መፃህፍት ላይ እንኳን ደህና መጡ።

የእርስዎ ቤተ መፃህፍት ላይ እንኳን ደህና መጡ።

 

የዲሲ የሕዝብ ቤተመፃሕፍት ላይ (DCPL) እንኳን ደህና መጡ። 25 የሰፈር ቤተመፃህፍት አካባቢዎች እና ማዕከላዊ ቤተመፃህፍት ይገኛሉ። (ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ሚሞሪያል ቤተመፃሕፍት)። ንባብን የሚያበረታቱ፣ ዲጂታል ዜግነት፣ ጠንካራ ማህበረሰቦች፣ የአካባቢ ታሪክ እና ባህልን የሚያበረታቱ አገልግሎቶች፣ መፃጽፎች እና መርሀግብሮችን ለወጣቶች እና ለአዋቂዎች DCPL ድጋፍ ይሰጣል። የቤተመፃሕፍት አካባቢዎች ነፃ ዋይፋይ፣ ነፃ የኮምፒውተር፣ የፕሪንተር አገልግሎቶች፣ የማህበረሰብ መሰብሰቢያ ክፍል ቦታዎች እና የመፃሕፍት፣ መጽሔት፣ ጋዜጣዎች፣ ዲቪዲዎች እና ተጨማሪ ነገሮችን ይሰጣል። እኛ ጋር ሲደውሉልን ወይም ሲጎበኙን ጊዜ፣ ለእርስዎ ያለምንም ወጪ በሚቀርብ፣ የስልክ የማስተርጎም አገልግሎት በኩል በቋንቋዎ ሠራተኞቻችን ያግዝዎታል። የቤተ መፃሕፍት አገልግሎቶችን የእኛን ብሮሸር ያንብቡ፣ ወይም ለተጨማሪ መረጃ ከታች ያለውን አገናኝ ይምረጡ።

ሁሉም የመዘግየት የቤተመጽሀፍ ቅጣቶች ተሰርዘዋል እና የምትክ ክፍያዎች ተሻሽለዋል። እባክዎ ዝርዝሮቹን እዚህ ያንቡ።

ቤተመፃህፍቱን መጠቀም

የቤተመፃሕፍት ካርድ ያግኙ

በእርስዎ ቋንቋ የሚነበቡ ነገሮችን ያግኙ

ሳምንታዊ የተረት ጊዜዎች

 

የሥራ ሰዓታት እና ቦታዎች