የዊዛርድስ የክረምት ንባብ ውድድር

የዊዛርድስ የክረምት ንባብ ውድድር

የዊዛርድስ  የክረምት  ንባብ ውድድር
በዚህ ክረምት የ DC የህዝብ ቤተ-መፃህፍት፣ ዋሽንግተን ዊዛርድስየአሌክሳንድሪያ ቤተ-መፃህፍት እና የፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ መታሰቢያ ቤተ-መፃህፍት ሥርዓት ከክረምት ውድድር ጋር ንቁ ሆነው እንዲቆዩ እና እንድትሳተፉበት ቤተሰብዎን ይጋብዛሉ! ከ ጃንዋሪ 1 - ማርች 31፣ ዕድሜያቸው ለትምህርት-የደረሰ ህፃናት እና ታዳጊዎች (ዕድሜያቸው 5-19 የሆነ) መመዝገብ እና ለደስታ ማንበብን፣ የመገናኛ ምናባዊ ዝግጅቶች መቀላቀልን፣ ከቤተ-መፃህፍት ማህበረሰብ ጋር ጊዜ ማጋራት እና መገናኘትን እና በአካል ንቁ ለመሆን አዝናኝ የሆኑ መንገዶች መፈለግን የሚያበረታቱ ባጆችን ማግኘት ይችላሉ። ቤተሰብዎ የሚወዱትን እና ዓመቱን ሙሉ ወደ መደበኛ ስራዎ መጨመር የሚችሏቸው ጤናማ ልምዶችን ለማግኘት የክረምት ውድድር ታላቅ መንገድ ነው።

ይመዝገቡ

ይመዝገቡበ ቢንስታክ በኩል ይመዝገቡ። ያለፉ የንባብ መርሀግብሮች ውስጥ ተሳትፈው ከሆነ፣ በተጠቃሚ ስምዎ እና የይለፍ-ቃልዎ አካውንትዎ ውስጥ መግባት ይችላሉ። ኢሜይልዎ በቅርብ የተሻሻለ መሆኑን ያረጋግጡ፣ ቤተ-መጻህፍቱ እና ዊዛርዱ ስለ ሽልማቶች የሚያሳዉቁዎት መንገድ ስለሆነ። ለመመዝገብ ተቸግረዋል? ኢሜይል ያድርጉልን ወይም በጎረቤትዎ ውስጥ የሚገኝ ቤተ-መጻህፍትን ያግኙ። ቢንስታክ መጠቀም አቅቶዎታል? ውድድሩን ለመቀላቀል ይህንን የጨዋታ ገበታን አውርደው ያትሙ እና መመሪያዎቹን ይከተሉ።

ባጆችን ያግኙ

ባጆችን ያግኙአንዴ ለክረምት ውድድር ከተመዘገቡ በኋላ ቢንስታክ ውስጥ ወይም የወረቀት የጨዋታ ገበታዎን በመጠቀም ባጆችን ማግኘት መጀመር ይችላሉ! የእለት ተእለት ተግባራትዎ ውስጥ ንባብ ለመጨመር፣ በአካል ንቁ ሆነው ለመቆየት አዝናኝ መንገዶችን ለመፈለግ፣ ተላላቅ የምናባዊ ዝግጅቶችን ላይ ለመገኘት እና እንደውም ዝም ብለው ከቤተ-መፃህፍቱ ማህበረሰብ ጋር በመገናኘትዎ ባጆች ይኖሩዎታል። የሚያገኙት እያንዳንዱ ባጅ ከዋሽንግተን ዊዛርድስ ሽልማቶችን ለማሸነፍ አንድ እርምጃ አቅርቦ ያስቀምጥዎታል።

ሽልማቶችን ያሸንፉ

ሽልማቶችን ያሸንፉውድድሩን ለመጨረስ የንባብ ባጁን እና ቢያንስ ሁለት ሌሎች ባጆችን ያግኙ። ከዚያ ከሰኞ፣ ማርች 15 - ዓርብ፣ አፕሪል 9፣ ከዋሽንግተን ዊዛርድስ የመጨረስ ሽልማትን ለመሰብሰብ በአቅራቢያዎ/ጎረቤትዎ ውስጥ የሚገኝ ቤተ-መጻህፍትን መጎብኘት ይችላሉ። እንዲሁም እንደ መለያዎች እና የተለየ የዲጂታል ልምዶች የመሰሉ ልዩ ተላላቅ ሽልማቶችን ለማሸነፍ የ ሐሙስ፣ አፕሪል 1 የእጣ ማውጫ ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋል።


ከቤተ-መፃህፍቱ ባጆችን ማግኘት

የክረምት ውድድር ባጆችዎን እንዲያግኙ እርስዎን ለመርዳት ሁሉም የሚፈልጉትን ነገር አለን! ለያንዳንዱ ዕድሜ እና ፍላጎት ከሚያስደስቱ ንባቦች፣ እስከ ምናባዊ ዝግጅቶች፣ ኦንላይን ለማጋራት እስከሚሆኑ እድሎች፣ የቤተ-መፃህፍትዎ ካርድ ለስኬት ያቅርብዎታል። የቤተ-መፃሕፍት ካርድ የለዎትም? ሀሳብ አይግባዎት! ዛሬዉኑ ለካርድ እንዴት እንደሚመዘገቡ ይማሩ

 
ማንበብ

ቤተ-መጻህፍቱ የማንበብ ግቦችዎን ለመምታት የሚረዱዎት ብቻ ሳይሆን፣ እንዲሁም የተወሰኑ አዲስ ተወዳጅ ነገሮችን እንዲያገኙ ሊረዱዎት የሚችሉ ለሁሉም ዕድሜ ቡድን የሚሆኑ ገራሚ የንባቦች ዝርዝርን አንድ ላይ ሰብስቧል።

ሕፃናት (5-12)
ለልጆች የሚሆኑ መጽሃፎች
ለልጆች የሚሆኑ የኤሌክትሮኒክ መጽሃፎች እና የኤሌክትሮኒክ የድምጽ መጽሃፎች

ታዳጊዎች (13-19)
ለታዳጊዎች የሚሆኑ መጽሃፎች
ለታዳጊዎች የሚሆኑ የኤሌክትሮኒክ መጽሃፎች እና የኤሌክትሮኒክ የድምጽ መጽሃፎች

ምናባዊ መርሀግብሮች

ቤተ-መጻህፍቱ በሳምንቱ በያንዳንዱ ቀን ሊባል የሚችል፣ ሊደሰቱባቸው የሚችሉ ከምናባዊ የቤተሰብ ኮንሰርቶች እስከ D-I-Y የእጅ ሥራ አውደ ጥናቶች እና ሌሎች ብዛት ያላቸው ምናባዊ መርሀግብሮች አሉት። ነገር ግን የ DC የህዝብ ቤተ-መጻህፍት ምናባዊ መርሀግብሮችን የሚያገኙበት ብቸኛው ቦታ አይደለም! በሙሉ የክረምት ውድድር ውስጥ አጋር ቤተ-መፃህፍቶቻችን የሆኑ፣ የአሌክሳንድሪያ ቤተ-መፃህፍት እና የፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ መታሰቢያ ቤተ-መፃህፍት ሲስተም እንዲያዩ እና ሙሉ የ DMV መዝናኛን እንዲቀላቀሉ እናበረታታዎታለን።

በዚህ ሳምንት ምን ምን ዝግጅቶች እየመጡ እንደሆነ ይመልከቱ!

ንቁ ሆኖ መቆየት ሰውነትዎን ጤናማ አድርጎ ማቆየት ብቻ ሳይሆን አዕምሮዎንም ጭምር እንደሚረዳ ያውቁ ኖረዋል? እዉነት ነው! የአካል እንቅስቃሴ በትምህርት ቤት ውስጥ የበለጠ እንዲማሩ እና የተሻለ እንዲሰሩ የሚያደርግዎት እንዲያተኩሩ እና ትኩረት እንዲሰጡ ሊረዳዎት ይችላል(ወይም የጨዋታዎ ቀጥሎ ያለውን ደረጃ እንዲደርሱ ይረዳዎታል!)። ሰውነትዎን ለማንቀሳቀስ የተወሰኑ ተላላቅ መንገዶችን ከ ዋሽንግተን ዊዛርድስ እና #FITDC ይመልከቱ!

የአካል ብቃት ቪድዮዎች
ዊዛርድስ በየእሮብ ቀናት ይሰራል።
#FITDC ለቤተሰቦች እና ልጆች የአካል ብቃት ጠምዛዛ መስመርን ያሰፋል።

በዚህ ክረምት ቤት ልንቆይ እንችላለን ግን ያ ማለት በኦንላይን ከእርስ በእርስ መገናኘት አንችልም ማለት አይደለም! የዋሽንግተን ዊዛርድስ እና ቤተ-መጻህፍቱ ከእርስዎ መስማት እና በክረምት ውድድር በምን እየተደሰቱ እንዳሉ ማወቅ ይፈልጋሉ።

ቤተመጽሀፍቱን ይከታተሉ በ
ኢንስታግራም
ትዊተር
ፌስቡክ

የ ጁኒየር ዊዛርድስን ይከታተሉ በ
ኢንስታግራም
ትዊተር

 

 

 




























































ተጨማሪ እየፈለጉ ነዎት? ለ ልጆች ወይም ታዳጊዎች የቤት ሥራ ዕርዳታ እየፈለጉም ሆነ፣ ለርቀት ትምህርት ተጨማሪ ቁሳቁሶችን ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ፣ ወይም ቤተ-መጻህፍቱን ወደ ቤት ለማምጣት አዝናኝ መንገዶችን ለማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ፣ የ DC የህዝብ ቤተ-መጻህፍት ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ 24/7 በኦንላይን ክፍት ነው!